የልገሳ አማራጮች

Support Our Cause

ለቤተክርስትያን ስጦታ ለማድረግ የሚከተሉት 3 አማራጮች ቀርበዋል። የቀረቡት አማራጮች ትክክለኛነታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ የእርስዎ መረጃ ደህንነትም የተጠበቀ ነው። የሚያስገቡት የክፍያ መረጃም ስጦታውን ከሰጡ በኋላ በዚህ ገፅ ላይ ቀሪ ሆኖ አይቀመጥም።

"ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ" ማቴ . 6 : 20

በፌስቡክ

  • ወደቤተክርስቲያናችን የፌስ ቡክ ገፅ ይህንን በመንካት ይሂዱ –› Facebook Page

  • በፌስ ቡክ ገፁ በቀኝ በኩል ከላይ የሚታየውን ‘Donate’ የሚለውን አማራጭ ይንኩ

    Image for በፌስ ቡክ ገፁ በቀኝ በኩል ከላይ የሚታየውን ‘Donate’ የሚለውን አማራጭ ይንኩ
  • የሚሰጡትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ

    Image for የሚሰጡትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ
  • የሚሰጡት ስጦታ ለአንድ ጊዜ ከሆነ ‘One Time Donation’ የሚለውን ይምረጡ፤ በየወሩ የሚሰጥ ከሆነ ግን ‘Monthly Donation’ የሚለውን ይምረጡ

  • ከቀረቡት የክፍያ አማራጮች አንዱን ይምረጡ፤ የፔይፓል ተጠቃሚ ከሆኑ Paypal የሚለውን ምርጫ ይከተሉ፤ ፔይፓል ተጠቃሚ ካልሆኑ በክሬዲት ካርድዎ ለመጠቀም ‘Add New Card’ የሚለውን ይንኩና የካርድ ቁጥርዎን ያስገቡ

  • በመጨረሻ ከገፁ ታች የሚገኘውን አረንጓዴ የልገሳ አማራጭ ወይም Donate የሚለውን ይጫኑ

በፔይፓል ወይም በክሬዲት ካርድ

  • Sበዚህ ገፅ ላይ የሚገኘውን Donate የሚለዉን በመጫን የሚከተሉትን በቅደም ተከተል ያድርጉ

  • የሚሰጡትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ፤ ስጦታውን በየወሩ መስጠት ከፈለጉ ‘Make this a monthly donation’ የሚለውን ይጫኑ አለበለዚያ ይህንን ምርጫ ሳይመርጡ ይቀጥሉ

    Image for የሚሰጡትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ፤ ስጦታውን በየወሩ መስጠት ከፈለጉ ‘Make this a monthly donation’ የሚለውን ይጫኑ አለበለዚያ ይህንን ምርጫ ሳይመርጡ ይቀጥሉ
  • ስጦታውን ለመስጠት የፔይፓል ወይም ክሬዲት ካርድ አማራጭን ይምረጡ

  • በመቀጠል ለኦዲት ያመች ዘንድ አድራሻዎን ለቤተ ክርስቲያናችን “Share your mailing address” የሚለዉን ይጫኑ

    Image for በመቀጠል ለኦዲት ያመች ዘንድ አድራሻዎን ለቤተ ክርስቲያናችን “Share your mailing address” የሚለዉን ይጫኑ
  • የክሬዲት ካርድ አማራጭን ከተከተሉ የክሬዲት ካርድ ቁጥርዎንና አድራሻዎን ይጠይቅዎታል፤ ተፈላጊውን የካርድዎን መረጃ አስገብተው ‘Donate Now’ የሚለውን በመጫን ስጦታውን ይፈፅሙ

በጥሬ ገንዘብ ወይም በካሽ

  • ዘወትር እሁድ ከቅዳሴ በኋላ በአዳራሹ በር ፊት ለፊት ለሰበካ ጉባዔ ሂሳብ ክፍል መክፈል ይችላሉ። እግዚአብሔር ይስጥልን።